ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 9 ወራት የተሰሩ ተግባራትን በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ የተከናወኑ ተግባራት በሰነድ የቀረበ ሲሆን በኦን ላይን ሰርተፊኬሽን አገልግሎት ፣ የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፣ ህገ ወጥ ግንባታ መከላከል ለሚቀርቡ የግንባታ ፍቃዶች በስታንዳርዱ መሰረት በመስጠትና ተከታታይነት ያለው ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም በ10ሩም ወረዳ ላይ የሚከናወኑ ተግባራት በወጣላቸው የግንባታ ፈቃድ ስታንዳርድ መከናወናቸው የመንገድ ዳር የውበት ስራዎችን መስራቱን በሪፖርቱ ተገልጿል። የክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ ባለፉት 9 ወራት ጽ/ቤቱ የክፍለ ከተማውን ነዋሪ በየደረጃው የሚጠይቃቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሊፈቱ የሚያስችሉ እና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንዲሁም ለማዘመን የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው በቀጣይም የተጀመሩ እና የተሻሻሉ አገልግሎቶችን አጠናክረን በማስቀጠል እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት በመታገል ከባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ በመስራት ለህብረተሰባችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም በመንገድ ዳር የሚገኙ የመንገድ ዳር አካፋዮችና ህንጻዎችን በስታንድርድ የማስዋብ ስራ በተለያዩ ወረዳዎች የተሰራበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በባለፉት 6 ወራት የላቀ አፈጻጸም ላመጡ ወረዳዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡